ዝክረ!

 

የሰው   እድሜ ፍጳሜ

ቅንጣት ታክል እጃሜ።

ባሕር ተሻግሬ

ሳይውጠኝ  ዓሳ ጉማሬ

ኑሮ ከባድ መራራ ተሸክሜ

ላቤን ኣንጠፍጥፊ ደሜ

ተራራ ወጥቸ ደክሜ

ገና እፎ ሳልል ተጋድሜ

ያፈራሁት ሳልቀምስ ደግሜ

ኣሎህ ኣሎህ ሰል ገና

ጎንበስ ብየ ቀና

ነገር ሳሰላስል፤

ስወድቅ፤ሰሰቆስል

ስነሳ ሰውመስል፡

ያገር ቤት ትዝታ

የዘመድ ናፍቆት በሽታ

በነጭ ትምክሕት፤ ድንፋታ

ባድርይ ኡምቩልታ፤ ጋጋታ

እንሆ፤ ልቤ ተፈታ!

 ባዩቶዋር ኣፈርም በረታ

ከርታታውን እኔን ሲረታ

ዋጥ ኣጎ ሊበላኝ ባንዳፍታ

ይታይ'ለ ኣፍን ከፍቶ ደረቱን ስመታ።

 

 

ኃይለሥላሴ ግርማይ

20/10/2007